Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በ2014 ዓ.ም የምርት ዘመን ከ198 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል-ቢሮው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል በ2014 ዓ.ም የምርት ዘመን ከ198 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን  የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ የክልሉን የ2013 ዓ.ም የግብርና ስራ እንቅስቃሴን  እና ቀጣይ እቅዶችን አስመልክቶ  መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው በክልሉ በ2014 ዓ.ም የምርት ዘመን ለማረስ እቅድ ከተያዘው 6 ነጥብ 3 ሚሊየን  ሄክታር መሬት ውስጥም 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬቱን በክላስተር ለመሸፈን መታቀዱን ተናግረዋል ።

ለዚህም 966 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር፣ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ መዘጋጀቱን የገለፁት ቢሮ ኃላፊው 2 ሺህ ትራክተሮች እና ከ270 በላይ ኮንባይነሮችን ለአርሶ አደሮች እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል።

መስኖን በመጠቀም ስንዴ የማምረት ስራውም በቀጣይ አመት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ይህም ከቀጣይ ዓመት የምርት ዘመን ጀምሮ ከውጪ የሚገባውን ስንዴ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ በሚመረተው ስንዴ ለመተካት ያስችላል ነው ያሉት።

በዘንድሮ አመትም ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት 183 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት ኃላፊው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን በተመለከተም ክልሉ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱንና በቀጣይም አጠናክሮ የሚሰራበት ዘርፍ መሆኑን አንስተዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.