Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)- አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በኮቪድ-19 ምክንያት በተወለደ በ50 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።

ዘገባው ኢብኮ ነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.