Fana: At a Speed of Life!

ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ለወጣው ጨረታ 6 ዓለም ዓቀፍ የቴሌኮም ድርጅቶች ሰነድ አስገቡ፡፡

የጨረታ ማስገቢያው ጊዜ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

በዚህም ለሁለቱ አዲስ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶች ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ ፣ቮዳኮም ከከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን እና ኤምቲኤን ግሩፕ ከደቡብ አፍረካ ሰነዶቻቸውን ማስገባታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የተጫራቾችን ስም እና ብዛት ይፋ ያደረገ ሲሆን የሚሰጡት ሁለት ፈቃዶች አሸናፊዎች የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን በተረከባቸው የጨረታ ሰነዶች ላይ የሚያከናውነውን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ግምገማዎች ካጠናቀቀ በኋላ የሚገለፅ ይሆናል ተብሏል::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.