Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ19 ባላንጣዎቹ ህንድና ፓኪስታንን በጋራ እንዲቆሙ አድርጓቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ ለተከታታይ ሶስተኛ ቀን ዓለም ላይ ከፍተኛውን የኮሮና ቫይረስ ተያዦችን ቁጥር አስመዝግባለች።

በቫይረሱ የሚያዙና ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ በህንድ የኦክስጅን እና የአልጋ እጥረት እንዲያጋጥም አድርጓል።

ይህን ተከትሎም በርካታ ሀገራት ከህንድ ህዝብ እና መንግስት ጎን መሆናቸውን በመግለፅ ሰው ሰራሽ መተንፈሻን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ፓኪስታናውያን ከህንድ ህዝብና መንግስት ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ያሳዩት የትዊተር ዘመቻ የተለየ ሆኗል።

በካሽሚር ግዛት የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ሁለቱ ሀገራት በተደጋጋሚ ጦር ተማዘው የነበረ ሲሆን አሁንም በጠላትነት የሚተያዩ ጎረቤት ሀገራት ናቸው።

ሆኖም ፖኪስታናውያን ከህንድ ጋር ከባድ ልዩነት ቢኖራቸውም ከህንድ ጋር እቆማለሁ በሚል መሪ ቃል የትዊተር ዘመቻ ማድረጋቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ከህንድ ጋር መቆማቸውን በመግለፅ በኮቪድ19 ህመም ላይ የሚገኙት በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በዚህ የፓኪስታናውያን የትዊተር ዘመቻ ታዋቂ ሰዎች ፣ ማህበራዊ አንቂዎች ፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና በመላው ፓኪስታን የሚገኙ ዜጎች ለህንዳውያን የአጋርነት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.