Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 14 ቀን ባለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ መያዙን አስታወቀ፡፡

በገቢ ኮንትሮባንድ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሃኒት፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጥ፣ የመዋቢያ ቁሳቁሶች፣ መለዋወጫ፣ ሲጋራና የተለያዩ የጦር መሳሪያ መሆናቸው ነው የገለጸው፡፡

በወጪ ኮንትሮባንድነት የተያዙት ደግሞ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያወጣሉ የተባሉ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የልዩ ልዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ፣ ሀሺሽና ቡና ናቸው፡፡

ዕቃዎቹ የተያዙት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በተለያዩ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዛቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ 21 ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ እንደሚገኝ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.