Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸው የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል የመንግስት እና የፓርቲ የሶስተኛው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ የሶስተኛ ሩብ አመት የስራ ዘመን በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ጠንካራ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በክልሉ በመስኖ ልማት ስራ እየለሙ የሚገኙ ስንዴ፣ አቮካዶ እና የማር ምርትን ለአብነት ተጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ በተጓዳኝ የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህልም እያደገ መምጣቱን ኦቢኤንን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.