Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን ጋጮባባ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ዘርፍ አስታወቀ።

የዘርፉ ሃላፊ አቶ ኢዮብ ዳርጻ እንደገለጹት፥ በወረዳው ላካ ቀበሌ ሚያዝያ 16 ሌሊት ስምንት ሰዓት አካባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቀበሌው በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋው ተከስቷል።

ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪም 14 አባወራዎች ከ70 ቤተሰቦቻቸው ጋር መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል።

በአደጋው ስምንት የቤት እንስሳት መሞታቸውንና በ2 ነጥብ 8 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙንም ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት በአደጋው ምክንያት ከቤታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በዳስ ውስጥ ተጠልለው የአካባቢው ህብረተሰብ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝም አመላክተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ደርሶ በላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በስፍራው ተገኝተው በማጽናናት ለአንድ ወር የሚሆን ስንዴ፣ በቆሎና የምግብ ዘይት እንዲደርሳቸው ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም በአካባቢው የወል መሬት በባለሙያ የመለየት ስራ እየተካሄደ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.