Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማዕከል ከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈጣን መመርመሪያ መሣሪያዎች የተደራጀ የኮቪድ-19 የምርመራ ማዕከል በአዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፈተ፡፡

ይህም የአየር መንገዱ ደንበኞች በረራቸውን ከመጀመራቸው በፊት እንዲመረመሩና እና ውጤታቸውን እንዲያውቁ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

አየር መንገዱ ከቻይናው የባዮቴክ ግዙፍ ኩባንያ፣ ከቢጂአይ ዘረመል ጥናት ኩባንያ ቅርንጫፍና ከቢጂአይ ሄልዝ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው የኮቪድ-19 የምርመራ ማዕከሉን የከፈተው፡፡

ማዕከሉን ስራ የማስጀመሪያ ስምምነቱን አስመልክቶ በናይጄሪያ የፊርማ ስነስርአት የተካሄደ መሆኑን ኦልአፍሪካን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኮቪድ-19 ምርመራ ማዕከሉን የተከፈተው በአዲስ አበባ በኩል ለሚጓዙ ተሳፋሪዎች ሲሆን፤ ማዕከሉ በቀን 1 ሺህ የኮቪድ-19 ምርመራዎች የማካሄድ አቅም እንዳለው ገልጿል፡፡

ውጤት በሶስት ሰዓታት ውስጥ የሚደረስ ሲሆን፤ ምርመራ እና ውጤት ለመጠበቅ የሚወስደውን ጊዜ በመቀነስ የበረራ ሰዓት እንዳይዘገይ የሚያደርግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.