Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚሰሩ እጆች ይበረታታሉ በሚል ሁለተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን እና ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ጋር በመሆን ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛሩን ከፍተዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጅ ኤግዚቢሽን እና ባዛራት አምራቹን እና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን በማቃለል ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
መሰል ኤግዚቢሽን እና ባዛሮች ከተለመደው ጊዜያዊ አሰራራቸው ተላቀው በዘላቂነት የገበያ ትስስር ሊፈጠርላቸው እንደሚገባ ተናግረው የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል ።
በሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ280 በላይ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን ለቀጣይ ሰባት ቀናት የሚያቀርቡ ሲሆን ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገበያ ትስስር እንደሚፈጠርላቸው መገለፁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.