Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት በጁባ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት ክብረ-በዓል የሃይማኖት አባቶች፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት እና በተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጁባ ተከብሯል።

በደቡብ ሱዳን የኢፌዴሪ አምባሳደር ነቢል ማህዲ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጁንታው የፈጸመው ጥቃትን ተከትሎ ለሠራዊቱ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ፣ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና ለሌሎችም ሃገራዊ ጥሪዎች ለተሰጡ ምላሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም የህዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አልፎም የአፍሪካ ፕሮጀክት ነው ያሉት አምባሳደሩ፥ ኢትዮጵያ ከታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት ጋር ያላትን ልዩነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት አፍሪካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ እየሠራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ 600 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያህል በቦንድ ግዥና በስጦታ ማበርከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ተሳታፊዎችም ለግድቡና ለሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ በቀጣይነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.