Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራሊዝም ሥርዓት ግንባታን ለማጠናከር በህዝብ ዘንድ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ትኩረት ያሻዋል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ግንባታን ለማጠናከር እንዲቻል የህዝቡን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ ብዙ መስራት ይገባል” ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።
በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ”ፌዴራሊዝምና የሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሃሳብ ምሁራን የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኃይለየሱስ ታዬ እንዳሉት፤ የፌዴራል ሥርዓቱ በህግ መንግስት ፀድቆ ከመዋቀር ባለፈ አተገባበር ላይ ክፍተት ነበረበት።
የፌዴራል ስርዓት ላይ ከፅንሰ ሃሳብ ጀምሮ የመንግስት አስተዳደር እና አተገባበር እንዲሁም ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ምን መሰራት አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ክፍተት እንዳለ ጠቅሰው፤ በቀጣይ ማህበረሰቡ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ የሚታየውን ችግር መፍታት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የህግና ፌዴራሊዝም ኮሌጅ መምህር ዶክተር መሀመድ ደጀን ማህበረሰቡ ስለፌዴራል ስርዓቱ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ በየወቅቱ የሚነሱ ግጭቶችን ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በኮተቤ ሚትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ የህግና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዶክተር አየነው ብርሃኑ በበኩላቸው በስርዓቱ ትግበራ ላይ ችግር እንደነበረበት አንስተው፤ ስርዓቱ ሰላም ከማስፈን እና ግጭት ከመቀነስ አኳያ የነበረው ሚና አነስተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።
የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚረዱ ውይይቶችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የውይይት መድረኩ በፌዴራል ስርዓት አተገባበር ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.