የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ለ 5 ሺህ እስረኞች ምህረት አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሁሉ የአንድነት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ 5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ታራሚዎች ምህረት አደርገዋል።
ፕሬዚዳንቷ ከእስር የተፈቱት ታራሚዎች ማህበረሰቡን እንደገና ሲቀላቀሉ ማረሚያ ቤት ያገኟቸውን ትምህርቶች በተግባር ላይ እንዲያውሉ እና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ አሳስበዋል ፡፡
የአንድነት በዓል ሚያዚያ 26 ቀን 1964 ታንጋኒካ እና ዛንዚባር ወደ አንድነት በመምጣት የታንዛኒያ ሪፐብሊክን የመሰረቱበት ዕለት ነው ፡፡
በየዓመቱ በአንድነት በዓል ቀን ለታራሚዎች ምህረት ማድረግ የተለመደ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!