Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ የምርጫ ነክ አለመግባባቶችን ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ምርጫ ነክ አለመግባባቶችን ለመከላከል የሚያስችል 13 አባላት የተካተቱበት ግብረ ኃይል ተቋቁሟል።

በግብረ ኃይሉ በአባልነት ከተካተቱ መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የሴቶች ፌዴሬሽንና የጸጥታ አካላት፣ የአካል ጉዳተኞች ማህበር፣ የሲቪክ ማህበራትና የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎችና መገናኛ ብዙሀን እንደሚገኙበት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ታጠቅ ተፈራ እንደገለጹት፥ ግብረ ኃይሉን ማቋቋም ያስፈለገው ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ነው።

ግብረ ኃይሉ የስጋት መረጃዎችን አስቀድሞ በመተንተን የመከላከልና ችግሮች ሲከሰቱም ፈጥነው መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰራ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.