Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ያሉ ልዩነቶች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ይፈታሉ የሚል ጠንካራ እምነት እንዳላት ሱዳን ገለፀች።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ውጤታማ እና ፈጣን መፍትሄ ላይ እንደሚደረስ እምነቷ መሆኑንን አስታውቃለች።

ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መሪ ቃል የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላትም ነው ሱዳን የገለፀችው።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወሳኙን እና አዲስ ሃሳብና አሰራር የሚመጣበትን የአፍሪካ ህብረትን እንደሚያደንቅ መግለፁን  ሱና ዘግቧል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሱዳን አቋሟን ለማስረዳት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኬንያ ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እንደምትልክ ገልጻለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.