አዲሱ የፌደራል ኢንተርፕራይዝ ልማት ስትራቴጂ ስራ አጥነትን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የፌደራል ኢንተርፕራይዝ ልማት ስትራቴጂ ዘላቂና አመርቂ ስራዎችን በመፍጠር የስራ አጥነት ምጣኔን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ።
ስትራቴጂው በፌደራል ስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን አማካኝነት የተዘጋጀ ነው::
ኮሚሽኑ የፌደራል ኢንተርፕራይዝ ልማት ስትራቴጂው ላይ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው::
በውይይቱ ላይ ኮሚሽነሩ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ጨምሮ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል::
ስትራቴጂው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ ያሉ ሌሎች አስተዳደራዊ አሰራሮችን የሚፈትሽና የሚያሻሽል ነው ተብሏል ::
ስትራቴጂው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀ ሲሆን ÷ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ያለውን ነባር ስትራቴጂ በጉልህ የሚያሻሽልና የሚቀይር መሆኑም ተገልጿል::
በዋናነትም እስካሁን ማነቆ ሆነው ዘርፉ እንዳያድግ ሲያደርጉ የቆዩ ችግሮች መለየታቸውንና መሻሻላቸውም በውይይቱ ላይ ተነስቷል::
ስትራቴጂው ተግባራዊ ከተደረገ በሚቀጥለው 10 አመት ውስጥ ለ20 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ስትራቴጂው ላይ ሊካተቱ የሚገባቸውና ትኩረት ሊስጥባቸው የሚገቡ ሀሳቦችን እያነሱ ይገኛሉ::
በዘቢብ ተክላይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!