Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ለበአል የሚሆን የእህል ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አማካኝነት ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት ስር ለሚገኙና ሌሎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 2ሺህ 400 ሴቶች ለመጪው በአል የሚሆን የእህል ድጋፍ ተደረገ።
ድጋፉ ከዚህ ቀደም ፕሬዚዳንቷ ድርጅቱን በጎበኙበት ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሳደረውን ጫና በመመልከት ለማገዝ ቃል በገቡት መሠረት የተገኘ እንደሆነም ተገልጿል።
በዚህም ድጋፉ በተለይም በዓል እየተቃረበ በመሆኑ የነበረባቸውን ጭንቀት በእጅጉ የሚያቀል እንደሆነም ነው የገለፁት።
አንዱጋ ትርፍ የሆነው የሌላውን ጓዳ የሚሞላ በመሆኑም ማህበረሰቡ ለመተጋገዝ ባህሉን ሳይዘነጋ የተቸገረ ጎረቤቱን ሊመለከት ይገባልም ብለዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከጤፍ ድጋፉ በተጨማሪም ለሌሎች ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናና መሰል ድጋፎች መደረጋቸው ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.