Fana: At a Speed of Life!

ጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ በቀጣዩ ግንቦት ወር የሙከራ ምርት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ በቀጣዩ ግንቦት የመጀመሪያ ቀናት የሙከራ ምርት ለማምረት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ አሰጌ ፋብሪካው በቀጣይ ግንቦት ወር መጀመሪያ ቀናት የሙከራ ምርት ለማምረት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ነው ብለዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ግንባታው መጓተቱ የተገለጸው የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ያሉበት ችግሮችን በማስተካከል ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ 87 በመቶ መድረሱም ተገልጿል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ የፋብሪካው የሙከራ ምርት ተከትሎ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በ2014 ዓ.ም ታኅሣሥ ወር ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ ለመግባት አቅደው እየሠሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ለሙከራ ምርት ሂደት 4 ሺህ ሄክታር አገዳ እየለማ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ወደ መደበኛ ምርት ሲገባም የግብዓት እጥረት እንዳይገጥም እየተሠራ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስኪያጁ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.