Fana: At a Speed of Life!

ስኬታማ የብር ኖት ቅያሬ ክንውን መካሄዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ስኬታማ የብር ኖት ቅያሬ ክንውን መካሄዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ባንኩ የብር ቅያሬ ክንውኑ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእውቅናና ምስጋና መርሀግብር እየተካሄደ ነው።

የብር ቅያሬው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ችግርና የእዳ ጫና ያቃለለ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ እስከ ሚያዝያ አጋማሽ ድረስ 7 ነጥብ2 ሚሊየን ዜጎች አካውንት የከፈቱ ሲሆን፤ ከ126 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወደ ባንክ ስርዓት መግባት ችሏል።

በተጨማሪም ከ185 ቢሊየን ብር በላይ አዲሱ ብር ተሰራጭቷል።

ለስኬታማ የብር ቅየራ ክንውን እገዛ ላደረጉ የእውቅናና ምስጋና መርሀግብር ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.