Fana: At a Speed of Life!

ቄራዎች ድርጅት ለትንሳኤ በዓል ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቄራዎች ድርጅት ለትንሳኤ በዓል ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከከተማ አስተዳደሩ አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጋር በመሆን በዓሉን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቅርተ ነጋሽ፤ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ህገወጥ እርድ እንደሚፈጸም ተናግረዋል።

ህገ ወጥ እርዶቹ በወንዞች አካባቢ፣ በሆቴሎች ጀርባና በተለያዩ ቆሻሻ ቦታዎች ስለሚከናወን ለጤና ስጋት መሆኑን ነው የገለጹት።

ከእንስሳት ወደ ሰው ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች ከማጋለጥ በተጨመሪ ሥጋው ስለሚመረዝ የጤና ስጋትነቱ የጎላ ሲሆን አሁን እየተስፋፋ ከመጣው የኮቪድ ስርጭትም አንፃር ጉዳቱ የከፋ ይሆናል ብለዋል።

ህገ ወጥ እርዱ ለህብረተሰቡ የጤና ስጋት ከመሆን ባለፈ ከተማ አስተዳደሩን በየዓመቱ በአማካይ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ እያሳጣው መሆኑም ተገልጿል።

ኮሚሽኑ ህገ ወጥ እርድ በሚያከናውኑ አካላት ላይ ከ15 ሺህ እስከ 25 ሺህ ብር ቅጣትና ከሁለት እስከ ሦስት ወር የእስር ቅጣት ማስቀመጡንም ተናግረዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ በየትኛውም ቦታ ህገወጥ እርድን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በበኩሉ ለመጭው የትንሳኤ በዓል ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማደረጉን አስታውቋል።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ለመጭው የንትሳኤ በዓል በድርጅቱ ከ4 ሺህ 500 እስከ 5 ሺህ የሰንጋ፣ የበግና የፍየል እርድ የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

የሥጋ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን የማደስና ዝግጁ የማድረግ፣ የቁም እንሳሰቱ ማደሪያና የእርድ ቦታን የማስተካከል ሥራ መሰራቱን ተናግርዋል።

በእርድ አገልግሎቱ ሉካንዳ ቤቶች ከሚያሳርዱት በተጨማሪ ለከተማዋ ነዋሪ የበሬ፣ ፍየልና በግ እንስሳት እርድ አገልግሎት እንደሚሰጥም አመልክተዋል።

በእርድ አገልግሎቱ ለበሬ 800 ብር፣ ለበግና ፍየል እያንዳንዳቸው 100 ብር ብቻ እንደሚያስከፍል ገልጸዋል።

የእርድ አገልግሎቱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ እንደሚከናወን ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.