Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከቶች ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች 350 ሺህ ዶላር ድጋፍ አሰባሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከቶች በትግራይና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተፈጠረው ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 350 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰቡን አስታወቁ።

የአህጉረ ስብከቶቹ ልኡካን አባላት ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጋር በሰብአዊ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ዙሪያ በመቐለ ከተማ ተወያይተዋል።

የተሰበሰበው ገንዘብ ከዳያስፖራው የተገኘ ድጋፍ መሆኑም ተመልክቷል።

ከልኡካኑ መካከል በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የካሊኒፎሪያ ሃገረስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁእ አቡነ ቴዎፍሎስ፤ በተፈጠረው ችግር ማዘናቸውን በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።

ልኡካኑ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርሲቲያን አህጉረ ስብከቶች ወክሎ እንደመጣ የተናገሩት ብፁእ አቡነ ቴዎፍሎስ፤ የተፈጠረው ችግር በአካል ለማየት በክልሉ እንደተገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.