Fana: At a Speed of Life!

ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጣናው የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ ኢትዮጵያ ካለችበት አሁናዊ ሁኔታ አንጻር ከቀጠናው ሃገራት ጋር ያሉትን የእርስ በርስ ግንኙነቶች በማጤን ለዘላቂ ሰላም ላይ በትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና የኢትዮጵያ ሰራዊት የአህገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡
አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል በበኩላቸው እንግሊዝ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር እንደ አዲስ በመቃኘት የጀመረቸውን የግንኙነት ምዕራፍ በመርህ ላይ በተመሰረተ አኳዃን ለማስኬድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ግልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል ፡፡
ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ስትራቴጂክ አጋርነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገርም በወታደራዊና የሰላም እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለሃገሪቱ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሂደትና ለቀጠናው ዙሪያ መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅኦ ያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይ ከሚካሄዱ ሃገራዊ ሁነቶችና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.