Fana: At a Speed of Life!

አዲስ የጎልማሶች ትምህርት ዲጅታል የመረጃ ሥርዓት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ሞጃ የተሰኘ አዲስ የጎልማሶች ትምህርት ዲጅታል የመረጃ ሥርዓት በኢትዮጵያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

ይህ ዲጅታል የመረጃ ሥርዓት በአፍሪካ ደረጃ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን የተመለከቱ ማንኛውንም መረጃዎች ለመውሰድና አዳዲስ መረጃዎችን ለመጫን የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ መሃመድ አቡበከር ይህ ዲጅታል መረጃ ሥርዓት በሀገራት መካከል ትስስር ለመፍጠር፣ በባለሙያዎች ዘንድ ልምድ ለመለዋወጥ፣ አንዱ ከሌላው የሚማማሩበት እንዲሁም አፍሪካዊ የሆኑ መሳሪያዎች እና ጥናታዊ ፅሁፎችን ለመለዋወጥ በቀላሉ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ለምታደርገው ለውጥ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

የዲ ቪ ቪ ኢንተርናሽናል ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አባተ “ሞጃ” የሚለው ህብረት ማለት ሲሆን በጎልማሶች ትምህርት ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት የሚያስተሳስር ነው ማለታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.