Fana: At a Speed of Life!

በበዓሉ ወቅት የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በበዓሉ ወቅት የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አጠቃቀምና ማብሰያዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ገንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በዓሉ ሲከበር ማህበረሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
በተለይም በምግብ ማብሰል ወቅት የኤሌክትሪክ ሃይል ጫና ሊፈጥር የሚችል የሶኬት አጠቃቀም እሳት ሊፈጥር ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
የጋዝ ሲሊንደሮች ከመለኮሳቸው በፊትና በኋላ የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችንም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፥ በተጨማሪም ሕብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት ከሰል፣ ሻማና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለበት መክረዋል።
የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የትንሳኤ በዓል በሚከበርበት ወቅት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይደርሱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።
ለበዓሉ 1 ሺህ 112 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 27 ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ 19 አምቡላንሶችና ሌሎች አደጋን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ዝግጁ መሆናቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.