Fana: At a Speed of Life!

ግብይቱ የተረጋጋና የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ልዩ ግብረ ሀይል ተዋቅሮ ቁጥጥር እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ግብይቱ የተረጋጋና የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ በሚያስችል መልኩ ልዩ ግብረ ሀይል አዋቅሮ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የፋሲካና የኢድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት እንደተናገሩት የምርት አቅርቦትና ስርጭት ችግር እንዳይኖር ለበዓሉ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ለሸማቹ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እየተሰራጨ ነው፡፡
በተጨማሪም ቢሮው በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ባስገነባቸው የቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት የበግ፣ ፍየልና በሬ ሽያጭ እንዲከናወን እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የገበያ ማዕከላቱን በፀረ ተዋህስያን የማፅዳት እና ሻጭም ሆነ ገዥ ወደ ማዕከላቱ ሲገቡ እራሳቸውን ከኮቪድ19 መከላከል የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡም የሚያጋጥሙ የንግድ ህግ ጥሰቶች ካሉ በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.