Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 115 የቀበሌ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማበህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 115 የቀበሌ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ለ22 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ሼድ አስረከቡ፡፡
በተጨማሪም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍል ከተማው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች እና ለፖሊስ አባላት የበሬ እና ሌሎች የምግብ በቁሳቁስ ስጦታ አበርክተዋል።
በዛሬው እለት ቀበሌ መኖሪያ ቤት ከተሰጣቸው የሀገር ባለውለታ ዜጎች መካካል ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ይገኙበታል ።
የከተማው ሀብት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በፍትሃዊነት ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
ዛሬ የመስሪያ ቦታ ሼድ የወሰዱ ኢንተርፕራይዞች በተሰጣቸው ቦታ ስራ ፈጥረው ሌሎች ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለከተማዋ እድገት እና ብልጽግና መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል ።
በተያያዘም ምክትል ከንቲባዋ ለ71 ሴክተር ተቋማት እና በ11 ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚሰሩ ከ1ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ለትንሳኤ በዓል የሚሆን ስጦታ ማበርከታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.