Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ያሰለጠናቸውን 387 እጩ መኮንኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለ8ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 387 እጩ መኮንኖች አስመረቀ፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዳመነ ዳሮታ በምርቃቱ ላይ  ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ ሲስተዋሉ የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቀረት የፖሊስ አባላት ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው።

በማረሚያ ቤቶች ሲስተዋሉ የነበሩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማረም የተለያዩ ተግባራቶች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

በህግ ቁጥጥር ስር ያሉ ዜጎችን የመብት አጠባበቅና አያያዝ በተመለከተ የማረሚያ ፖሊስ አባላትና አመራሮች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሆኑም በዛሬው እለት ለ8ኛ ዙር ለምረቃ የበቁት እጩ መኮንኖችም አላማው ይህንን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

የተቋሙን ተዕልኮ ለማሳካትና ቀደም ሲል የተስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሪፎርም ስራዎች ውጤት በሚያመጣ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ ገልጸዋል።

በተቋሙ የተጀመሩ ለውጦችን በማጠናከር የህግ ታራሚዎችን ሰባዊ መብት በማክበር የመስራት ሃላፊነት እንዳለባቸው ለተመራቂዎቹ ገልጸው ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም አሳስበዋል።

ለ8ኛ ዙር የሰለጠኑት እጩ መኮንኖች ለሶስት ወራት በአሌልቱ ማሰልጠኛ ተቋም የተለያዩ የመስክና የክፍል ውስጥ ትምህርትና ስልጠናዎችን ወስድዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 304 ወንዶችንና 83 ሴት እጩ መኮንኖች ሲሆኑ 265 ሰዓታት በክፍል ውስጥ እንዲሁም 117 ሰዓታት የመስክ ስልጠና ወስደዋል።

ማሰልጠኛ ተቋሙ ከዚህ በፊት በ32 ዙር በመሰረታዊ የማረሚያ  ፖሊስ ስልጠና በመስጠት ማስመረቁም ተመላክቷል፡፡

በምርቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር ጀነራል ዳመነ ዳሮታን ጨምሮ የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸነሮችም መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.