Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወቅቱን ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በበዓላት መዳረሻ ወቅት ከወትሮው በተለየ ጨምሮ የሚታየውን የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከትሎ የትራፊክ አደጋ እና ወንጀል እንዳይፈፀም ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ የፀጥታ ስራ እንደሚያከናውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውሷል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ÷ በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ እና የግብይት ስፍራዎች እና የዕምነት ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ኮሚሽኑ የወቅቱን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ በማውጣት ለአመራርና አባላቱ ግንዛቤ በማስጨበጥ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል፡፡

በተለይም በዓሉን ምክንያት አድርገው የገበያ አለመረጋጋትን ለመፍጠር ምርት በሚደብቁ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ለፖሊሳዊ አገልግሎትም ሆነ መረጃ እና ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 991 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 መጠቀም እንደሚቻል ያስታወሱት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ÷ ህብረተሰቡ በዓሉን ለማክበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችም ግርግሩን በመጠቀም ተመሳስለው ስለሚንቀሳቀሱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ  በማለት በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞት መግለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

በተለይም በግብይት፣ በመዝናኛ ስፍራዎች እና በዕምነት ተቋማት አካባቢ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.