Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ ተነስቶ ጎፋ ማዞሪያ- ጎተራ ማሳለጫ የሚዘልቀውን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ በመዲናዋ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተጀምረው በጥሩ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ካሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“ይህ ደግሞ የመሰረት ድንጋይ ብቻ ጥለን የምንሄድ ሳይሆን የተናገርነውን በተግባር እያሳየን መሆኑን የሚገልፅ የግንባታ ፕሮጀክት ነው” ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ፡፡
የመዲናዋን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለመመለስና አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ ቀን ከሌሊት መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 72 ነጥብ 3 በመቶ የግንባታ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከፑሺኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ድረስ ያለው ዋናው መንገድ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 320 ሜትር ርቀት የሚሸፍን የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ የዋሻ እና 100 ሜትር ርዝመት ያለው ተሸጋጋሪ ማሳለጫ ድልድይ ግንባታን አካቶ እየተሠራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.