Fana: At a Speed of Life!

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የእስያ ሃገራት አምባሰደሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ገለጻ ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ላደረጉ የእስያ ሃገራት አምባሳደሮች በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ገለጻ አደረጉ፡፡

የሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ፣ በህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር እና በመጪው ሃገራዊ ምርጫ ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል ከሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘም የተሻለ አፈጻጸም ቢመዘገብም በክልሉ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አንጻር ተግዳሮቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በክልሉ በጋራ ምርመራ ለማካሄድ የደረሱበትን ስምምነት እንዲያፋጥኑ ማሳሰቡንም ነው ያስታወቁት፡፡

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሱዳን ላነሳቻቸው ስጋቶች ምላሽ ማግኘቷን የጠቀሱት አምባሳደሩ በግብጽ በኩል ግን አሁንም የቅኝ ግዛት ውሎችን በማንሳት ድርድሩን መቋጫ እንዳያገኝ እየሰራች እንደምትገኝ ነው ያስረዱት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.