Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለ2 ሺህ 705 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ለ2 ሺህ 705 ታራሚዎች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው 56 ሴት እና 2 ሺህ 649 በድምሩ 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ በይቅርታ መለቀቃቸውን የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አለምሸት ምሕረቴ ተናግረዋል፡፡

አቶ አለምሸት በተለያዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው አንድ ሦስተኛ የእስራት ጊዜያቸውን የጨረሱ እና በማረሚያ ቤት የሥነ ምግባር ለውጥ ማሳየታቸው የተረጋገጠላቸው ታራሚዎች ናቸው በይቅርታ እንዲለቀቁ የተወሰነው፡፡

በጥቅሉ ሕጻን ይዘው የታሰሩ ሴቶችና ነብሰ ጡር እስረኞች ከሆኑ ደግሞ ከተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ አንድ አምስተኛውን ካጠናቀቁ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

የዕድሜ ልክ እስራት ከተፈረደባቸው መካከል 60 ዓመት የሞላቸው ወንዶች 12 ዓመታት በእስራት ከቆዩ፣ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ 55 ዓመት ሆኗቸው 10 ዓመታት ከታሠሩ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡

ይሁን እንጂ ይቅርታው ከ15 ዓመት በታች የሆነች ልጃገረድ አስገድዶ የደፈረ፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም በሙስና ወንጀል 10 ዓመትና ከዚያ በላይ እስራት የተፈረደባቸውን ታራሚዎች እንደማያካትት አስታውሰዋል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ መውጣት መጀመራቸውንም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.