Fana: At a Speed of Life!

ለትንሳኤ በዓል የተሻለ የውሃ ስርጭት እንዲኖር ተጨማሪ 10ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ያመርታል- የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለትንሳኤ በዓል የተሻለ የውሃ ስርጭት እንዲኖር ተጨማሪ 10ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ እንደሚያመርት የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ የትንሳኤ በአል በጥሩ ሁኔታ እንዲከበር እስከ ምሽት አምስት ሰዓት የሚሰሩ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
የከፋ የውሃ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ውሃ በፍጥነት ለማዳረስ ይቻል ዘንድ በየቅርንጫፉ እና በዋናው መስሪያ ቤት 18 በተጠንቀቅ የሚጠብቁ ቦቴዎችን አዘጋጅቷል፡፡
ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ ከፍተኛ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑ ተቋማት የተወሰነ የውሃ መጠን በመቀነስም ወደ ነዋሪዎች የማዳረስ ስራም ይሰራል፡፡
የተሻለ የውሃ ስርጭት ያለባቸው አካባቢዎች ውሃን በቁጠባ በመጠቀም ለሌላው እንዲዳረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መጠየቁን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.