Fana: At a Speed of Life!

የ2013 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ተለቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የ2013 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ተለቋል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በመሆኑም ተማሪዎች በዚህ http://result.neaea.gov.et/Home/Placement የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ የሚችሉ መሆኑን የከፍተኛ ሳይንስና ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በአካል መምጣት ሳያስፈልግ ቅሬታ ለማቅረብ ይህን https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7 የበይነ መረብ ጠቋሚ መከተል እንደሚቻል አስታወቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩም ተቋሙ አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.