Fana: At a Speed of Life!

መንግስት አፋጣኝ የዕለትና የመቋቋሚያ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው የአጣየ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት አፋጣኝ የእለት እና የመቋቋሚያ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በሰሜንሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ አጣየ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቦታው ተገኝቶ ባደረገው ቅኝት በከተማዋ በደረሰው ጥፋት ነዋሪዎቿ ቤት አልባ ሲሆኑ፤ የመብራት እና የውሃን መሰረተ ልማትን ጨምሮ በርካታ ውድመት ደርሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ከግለሰብ እስከ መንግስት ተቋም ደረስ ወድሞ ከጥቅም ውጭ መሆኑንም በስፍራው ቅኝት ያደረገው ባልደረባችን አረጋግጧል፡፡

በቦታውም ከፌዴራል እና ከመከላከያ የፀጥታ አካላት ውጭ በቦታው ተገኝቶ ችግሩን የተመለከተልን አካል የለም ሲሉም ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ አሁንም ስጋትና ፍርሃት እንዳለ ጠቅሰው፤ መንግስት አጥፊዎቹን ለህግ አቅርቦ ማስተማምኛ ሊስጠን ይገባል ሲሉም ያሳስባሉ።

መንግስት ወደነበርንበት እንድንመልስ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ሲሉም ጠይቀዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.