Fana: At a Speed of Life!

የሕንድ የኮሮና ቫይረስ ቀውስ ለአፍሪካ የማንቂያ ደውል ነው- የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪና መከላከያ ማዕከል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪና መከላከያ ማዕከል ሕንድ ያጋጠማት የኮሮና ቫይረስ ቀውስ ለአፍሪካ የማንቂያ ደውል ነው ሲል አስጠነቀቀ፡፡
የማዕከሉ ሃላፊ አፍሪካውያን የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ ፣ ትልልቅ ስብሰባዎችን ማስወገድ እንዲሁም የጤና ስርዓታቸውን ማሻሻል አለባቸው ብለዋል፡፡
እንደ ሃላፊው ገለፃ የአፍሪካ ሀገሮች በአጠቃላይ በቂ ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎች ፣ የሆስፒታል አልጋዎች እንዲሁም የኦክስጂን አቅርቦቶች የላቸውም፡፡
እንዲሁም 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ ያላት ህንድ ከአፍሪካ ጋር ተመሳሳይ የህዝብ ብዛት ያላት ቢሆንም አፍሪካ ደካማ የጤና አሰራሮች ያሏትና እንደ ህንድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መድኃኒቶችንና ክትባቶችን የማታመርት አህጉር ናት ብለዋል፡፡
በዚህም በሕንድ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር በአፍሪካ ቸላ ሊባል አይችልም ያሉ ሲሆን የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች እንዲሁም ህዝቦች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
ሁሉም የፖለቲካ እና የሃይማኖት ስብሰባዎች ቫይረሱ እንዲዛመት እድል ይሰጣሉ ያሉት ሃላፊው ለጊዜው መታገድ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡- አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.