Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ስናከብር የዕምነቱ አስተምህሮ የሚጠይቀውን መልካም ተግባር በመፈፀም በፍቅርና በመተሳሰብ መሆን አለበት -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ  ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት  አስተላልፈዋል።

ምክትል ከንቲባዋ   ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ÷ ይህንን ታላቅ ሀይማኖታዊ በዓል ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም የአብሮነት መንፈስ   መሆን አለበት ብለዋል።

ምክትል ከንቲባዋ አያይዘውም በዓሉን እኛ ስንበላ በልተው የማያድሩ ፤ እኛ ስንለብስ መልበስ ያልቻሉ  ወገኖቻችንን በማሰብና አለሁላችሁ በማለት  እንዲሁም የዕምነቱ አስተምህሮ የሚጠይቀውን መልካም ተግባር በመፈፀም በፍቅርና በመተሳሰብ  ከጎናቸው ልንሆንና ልናግዛቸው ይገባልም ነው ያሉት፡፡

የተቸገረን መርዳት እና ማፍቀር ከቀደሙ እሴቶቻችን የተማርነው በመሆኑ በዓሉን እንደ ሁልጊዜው በመረዳዳትና በአብሮነት እንድናከብር በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እጠይቃለሁም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.