Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ለማድረግ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ቱሪዝም ኢትዮጵያ ገለጸ።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ ÷ ኢትዮጵያን በቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሃገር አቀፍ ደረጃ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት የመስህብ ስፍራዎችን በማልማት ላይ ይገኛልም ብለዋል፡፡

በዚህም ገበታ ለሸገር ፕሮጀክትን ወደ ገበታ ለሃገር በማሳደግ በአማራ ክልል ጎርጎራ፣ በኦሮሚያ ወንጪና በደቡብ ኮይሻ ሀይቆችን የጎብኚ መዳረሻ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

“ገበታ ለሸገርን ወደ ገበታ ለሃገር እንዳሳደግነው ሁሉ ገበታ ለሃገርን ወደ ገበታ ለአህጉር በማሳደግ ኢትዮጵያ ሀብቷን በመጠቀም፥ እስከ አፍሪካ ገበያ አስፋፍታ ማሳየት እንደ ምትችል እናስመሰክራለን” ነው ያሉት፡፡

በዚህ መልኩ ሀገሪቱን በአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የፕሬስ ድርጅት ዘገባ ያመላክታል፡፡

ጎብኚዎችም ኢትዮጵያን እንዲመርጡ የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደና ሥልጠናዎችም እየተሰጡ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ስለሺ÷ የማስተዋወቅ ስራን የሚያዘምኑ ሥራዎች መሰራታቸውንና ትግበራዎቹ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚያስችሉም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.