Fana: At a Speed of Life!

ለዋርዴር ሆስፒታል 3 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል የዶሎ ዞን ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት ለዋርዴር ከተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ሶስት ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉ ዘመናዊ ህክምና አልጋዎች፣ ፍራሾችና ሌሎች ድጋፍ የሚሰጡ የህክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

የዋርዴር ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አህመድ ዴቅ አደም ጀማ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፉ የሆስፒታሉን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሳደግና ለአካባቢው ማህበረሰብ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዶሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዲሸኩር ሃሺ በበኩላቸው፤ ለዞኑ ጠቅላላ ሆስፒታል ድጋፍ ላበረከቱት ለኬይሪያ ዳያስፖራ ፎረምና ለከራማ የድጋፍ ድርጅት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሌሎች የማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የእነዚህን ዳያስፖራ ማህበራት አርአያ በመከተል በዞኑና በክልሉ እየተከናወኑ ባሉ መሰረ ልማት አውታሮች በሰፊው ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.