Fana: At a Speed of Life!

አሚሶም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የክብር ሜዳልያ ሸለመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ስር የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡

ሽልማቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ በነበራቸው የአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ያለመ መሆኑን አሚሶም አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ወታደሮቹ አልሸባብን ለመደምሰስ በተካሄደው ዘመቻ ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር በበለተወይኒ ሴክተር አራት ተሰማርተው ግዳጃቸው የተወጡ ናቸው፡፡

በአሚሶም የጂቡቲ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አብዲራህማን ሃሬድ፥ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች የሶማሊያን ደህንነት ለማስጠበቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ጊዜ፣ ጉልበትና ህይወታቸውን ለሰጡ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.