Fana: At a Speed of Life!

የትንሳኤ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብርና ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላትም ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ለበዓሉ በሰላም መከበር የከተማው ነዋሪ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉንም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡
የከተማውን ጸጥታ ለማስከበር በሚሰሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አስተላልፏል፡፡
በትራፊክ አደጋ ዙሪያ በበዓሉ ዋዜማ እና በበዓሉ እለት በደረሱ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኮሚሽኑ አስታውቆ ከወንጀል ድርጊት ጋር ተያይዞ በዓሉ በሰላም መከበሩን ገልጿል፡፡
ወደፊትም የከተማውን ሠላምና ጸጥታ ለማስከበር በሚሰሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ህብረተሰቡ ያልተቆጠበ ትብብሩ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪ ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.