Fana: At a Speed of Life!

እየጣለ ያለው ዝናብ ለመኸር እርሻ ዝግጅት ምቹ በመሆኑ አርሶ አደሩ ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል – የግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየጣለ ያለው ዝናብ ለመኸር እርሻ ዝግጅት የተመቸ በመሆኑ አርሶ አደሩ ጠንክሮ መስራት እንደሚኖርበት የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በሚኒስቴሩ የሰብል ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ግርማሜ ጋሩማ አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ የበልግ ወቅት ተጠቃሎ እየወጣ ላለባቸው አካባቢዎች ለሰብላቸው የደረሰላቸው ነው ብለዋል፡፡
ለመኸር ዝግጅት ማሳውን እያሰናዱ ላሉ አርሶ አደሮች ደግሞ መሬቱን በእርጥበት ለማራስ ምቹ ሆኖላቸዋል ብለዋል ።
በበልጉ ምርት የሚያነሱት አርሶ አደሮችም በፍጥነት እንዲዘጋጁ ብርታት የሚሰጣቸው በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ተናግረዋል።
የብሄራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ትንበያ ባለሙያ አቶ ታምሩ ከበደ ቀጣይ 10 ቀናት አሁን ያለው የዝናብ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
የዝናቡ በዚህ መቀጠልም አርሶ አደሩ ማሳውን ተመላልሶ እንዲቃኝ ይረዳዋልም ነው ያሉት፡፡
ዝናቡ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ድንገተኛ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቅሰው፥ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ያሉ ማሳዎች ላይ ዝናቡ ጉዳት እንዳያደርስ አርሶ አደሩ ጥንቃቄዎችን ሊያደርግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከዝናቡ ጋር ተያይዞ አረም ሊከሰት ስለሚችል የኬሚካል ዝግጅት ላይ አርሶ አደሩ እንዲያተኩርና የ10 ቀናት የዝናብ ስርጭት ትንበያ መረጃ እንዲከታተልም መክረዋል።
በሀይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.