Fana: At a Speed of Life!

ምርጫውን በሠላማዊ መንገድ ለማከናወን የለውጥ ስራዎች ተሰርተዋል – አቶ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስድስተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለማካሄድ የተለያዩ የለውጥ ስራዎች መከናወናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

አፈ-ጉባኤው የስድስተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ቅድመ-ዝግጅት አስመልክቶ ከአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት መንገድ የምርጫ ሕጉ መሻሻሉንና የምርጫ ቦርድ አባላት መመረጣቸውን ለታዛቢዎቹ አብራርተውላቸዋል፡፡

ምርጫው በተቀመጠለት የጊዜ መርሃ-ግብር እንዲከናወን የምርጫ ቁሳቁሶች ወደየምርጫ ጣቢያዎች እንደተጓጓዙ ጠቅሰዋል።

በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትም ሕጋዊ አሰራሮችና የጸጥታ አደረጃጀቶች እንደተዘረጉ አቶ ታገሰ ተናግረዋል፡፡

በጸጥታ ጉዳይ በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተራዝሞ የነበረው የመራጮች ምዝገባም በአሁኑ ወቅት ከሞላ ጎደል መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ምርጫውነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ታዛቢ ቡድኑ በቂ መረጃ ማግኘቱን አስረድተዋል፡፡

በምርጫው የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግና ሴቶች መራጭ ብቻ ሳይሆኑ ተመራጭም እንዲሆኑ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይም በአመራር ሰጭነት የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ እንደሆነ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.