Fana: At a Speed of Life!

ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቃለች፡፡

በሃገሪቱ ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2020 ድረስ ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች በኢቦላ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ወረርሽኙ በቫይረሱ ከተያዙ እና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት የነበራቸውን ከ1 ሺህ 600 የሚበልጡ ሰዎች በማሰስ መርክ የተባለውን የኢቦላ ክትባት እንዲወስዱ መደረጉን የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል፡፡

የቫይረሱ ምልክት የማይታይበትና ከበሽታው ባገገመ ህመምተኛ የሰውነት ፈሳሾች ውስጥ ቫይረሱ ሊቆይ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ቫይረሱ ከ2013 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት በምዕራብ አፍሪካ ወደ 11ሺህ ሰዎች ህልፈት መሆኑ ይነገራል፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኮሮና ቫይረስ በተጨማሪ የኢቦላ ዳግም መከሰት ስጋት ፈጥሮ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.