Fana: At a Speed of Life!

“የኢትዮጵያ ሳምንት” ከግንቦት 10 እስከ ግንቦት 16 ይከበራል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያ ሳምንት” ከግንቦት 10 ቀን እስከ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገለጸ።
ዝግጅቱ ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት እና ፀጋ በማስተዋወቅ ወደ ኢንቨስትመንት መቀየርን አላማው ያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡
“የኢትዮጵያ ሳምንት” በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐሳብ አመንጪነት ለሦስት ሴት ሚኒስትሮች የቤት ሥራ በመስጠት ዝግጅቱን ለማከናወን ሲሠራ መቆየቱም ተገልጿል።
በዚህም ሶስቱ ሴት ሚኒስትሮች ማለትም የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሣው፣ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እና የሴቶች፣ ወጣቶች እና ሕፃናት ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ በዝግጅቱ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በፌስቲቫሉ የሁሉም ክልሎች መገለጫዎች፣ ሀብት እና ፀጋቸው በቅርፃ ቅርፅ፣ በምሥል እና በተንቀሳቃሽ ምሥል በወዳጅነት አደባባይ ተዘጋጅቷልም ነው የተባለው።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከዝግጅቱ የሚገኘው ገቢ ለተፈናቃይ ዜጎች ማቋቋሚያ እንደሚውልም ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.