Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ሩሲያ በምስራቃዊ ሱዳን የጦር ሰፈር ለመገንባት ያስገባቻቸውን መሳሪያዎች እንድታስወጣ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ፖርት ሱዳን በተሰኘው ምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ሩሲያ የጦር ሰፈር ለመገንባት በማሰብ ያስገባቻቸውን መሳሪያዎች እንድታስወጣ ጠየቀች፡፡

ሁለቱ ሀገራት በህዳር ወር መጀመሪያ በፖርት ሱዳን የጦር ሰፈር መገንባት የሚያስችል ረቂቅ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በረቂቅ ስምምነቱ መሰረት ሩሲያ ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያላቸውን አራት የጦር መርከቦችና 300 የባህር ሃይል አባላቷን በሱዳን ወደብ ላይ ማስፈር እንደምትችል የሚገልጽ ነበር፡፡

ሆኖም ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ስምምነቱ ዕውን እንደማይሆን ነው ያሳዩት፡፡

በሱዳን የሩሲያ ኤምባሲ በይፋ እስካሁን ስለስምምነቱ መታገድ የተነገረኝ ነገር የለም ቢልም የሱዳን ባለስልጣናት ግን በፖርት ሱዳን ለሚገኙ ሩሲያዊ ሌተናል ጀነራል የመንግስትን አቋም ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለስልጣናቱ ሩሲያ በፖርት ሱዳን የገጠመቻቸው ወታደራዊ መሳሪያዎች፣ ራዳሮች እና የግንኙነት መሣሪያዎችን በሙሉ እንድታስወጣ ሌተናል ጀነራሉን መጠየቃቸውን ያስታወቁት፡፡

ይህን ተከትሎም የሩሲያ የጦር መርከብ በፖርት ሱዳን የሚገኙ መሳሪዎቹን ሳያስወጣ እንዳልቀረም ሱዳን ትሪቢዩን አስነብቧል፡፡

ሃገራቱ በኦማር ሃሰን አልበሽር አስተዳደር ዘመን ለሰባት ዓመታት የሚቆይ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

የሽግግር መንግስቱም ስምምነቱን በማስቀጠል በፖርት ሱዳን የጦር ሰፈር ግንባታውን እንድታካሄድ ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.