Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ አምባሳደር ለዐርበኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤፍጌኒ ተረክህን ለ80ኛ ጊዜ የሚከበረው የዐርበኞች ቀንን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1935 በፋሽስት ጣልያን ወረራ ከደረሰባቸው ሃገራት መካከል የመጀመሪያዋ እንደነበረች አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፋሽስት የደረሰባት ወረራም የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት አይቀሬነት የተነበየ ነበር ብለዋል፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ሀገራቸውን ከፋሽስት ነጻ በማውጣት ቀዳሚዎቹ ናቸው ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

በወቅቱ የነበረው አንድነት፣ የመንፈስ ጥንካሬና የነፃነት ፍላጎት ለድሉ ወሳኝ ሚና ነበርው ሲሉ ነው ያስታወሱት፡፡

በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በፋሽስት ሰለባ መሆናቸውን የጠቀሱት አምባሳደሩ የአሁኑ ትውልድ ይህንን መስዋዕትነት እንደሚያስብ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ድርጊቱ ዳግም እንዳይከሰት ትውልድ እንዲማርባት ታሪካዊ ድሉን ማሰብ ይገባል ማለታቸውን ከሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.