Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ሀዘን ገልጸዋል።

”ወንድማችን ለክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥ ለዓመታት ከቤተሰቡ ርቆ ለዓላማው ሙሉ ጊዜውን በመስጠት በፅናት ያገለገለ ጠንካራ አመራር ነበር” ብለዋል።

”የወንድማችን የአመራር አበርክቶዎች ታሪክ የማይዘነጋቸው ሲሆ፤ ይሄን የመሰለ ታላቅ ሰው በድንገት ማጣት ሃዘናችንን መራራ እና ጥልቅ ያደርገዋል” ሲሉም ገልጸዋል።

በአመራር ዘመኑ የደከመለትን በክልሉ የህግ የበላይነት እና ሰላምን የማረጋገጥ ቁልፍ ተልዕኮ በጓዳዊ ቅብብሎሽ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

በመጨረሻም ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የክልላችን አመራር እና ህዝብ መፅናናትን መመኘታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.