Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ  “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቀጥር 923/2008ን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከምክር ቤቱ ያገነኘው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.