Fana: At a Speed of Life!

የዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ ገፅ ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌስቡክ ገፅ ታግዶ እንዲቆይ የፌስቡክ ገለልተኛ የይዘት የቁጥጥር ቦርድ ውሳኔ አሳላፈ።

ፌስቡክን ጨምሮ ትዊተርና ዩትዩብ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ምክር ቤት (ካፒታል ሂል) ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አበረታተዋል በሚል እንዳገዷቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የፌስቡክ ገለልተኛ የይዘት የቁጥጥር ቦርድ በትራምፕ ላይ የተላለፈው እገዳ ይነሳ ወይስ ይቀጥል በሚለው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ በዛሬው ዕለት ተሰብስቦ እንደነበረ የተለያዩ መገኛኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በዚህም በዶናልድ ትራምፕ ላይ የተላለፈው እገዳ እንዲቀጥል የአካዳሚ ሰዎችን ፣ የህግ ባለሙያዎችን እና ሌሎችን ያካተተው ቦርድ ውሳኔውን አፅንቷል።

በርካታ ተከታዮች ከነበሯቸው ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የታገዱት ዶናልድ ትራምፕ በትናትናው ዕለት አዲስ  የግላቸውን ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.