Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  ኒጀር ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኒጀር ገቡ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኒጀር ኒያሚ ሲደርሱ የኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር ማማድ ኡሙዱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቷ ወደ ኒጀር የተጓዙት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከኒጀሩ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ባዞም ጋር ለመነጋገር ነው።

እንዲሁም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ እና ኢትዮጵያ ስለምታካሂደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ ያሉ አዳዲስ ጉዳዮችም ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ የያዘችውን አቋም እና ግድቡ ያለበትን ወቅታዊ ደረጃ በተመለከተም ከፕሬዘዳንቷ በተጨማሪ የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ መረጃዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኒጀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ተለዋጭ አባል ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

ኒጀር እንደ ተለዋጭ አባልነቷ በፀጥታው ምክር ቤት በየትኛውም የዓለም ሀገራት በሚኖሩ ግጭቶች ላይ የራስዋን አቋም የማራመድ መብት አላት።

በመሆኑም የፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የኒጀር ቆይታ ኒጀር ኢትዮጵያን በተመለከተ በፀጥው ምክር ቤት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ያስይዛታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.