Fana: At a Speed of Life!

በ49 ሚሊየን ብር ወጪ የተደራጀው የፊዚክስ ቤተ ሙከራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ49 ሚሊየን ብር ወጪ የተደራጀው የፊዚክስ ቤተ ሙከራ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ዴአ ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መመደቡን አስታውሰው ለዚህ ተግባር ተኮር ትምህርት አጋዥ የሆኑ ቤተ ሙከራዎችና ሰርቶ ማሳያዎችን መልሶ የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በቅርቡም ከፍተኛ ሀብት በመመደብ ስምንት ያህል የሳይንስ ቤተ ሙከራዎችን መልሶ የማደራጀት ስራ መከናወኑን ጠቅሰው፥ ከሰሞኑም ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው ያልነበሩ ዘመናዊ የፊዚክስ ቤተ ሙከራ ቁሳቁሶችን የማሟላትና መልሶ የማደራጀት ስራ መሰራቱን አውስተዋል።
ይህም የዩኒቨርሲቲው ከተመደበበት የትኩረት መስክና ልየታ ረገድ መሰረታዊና ተጨባጭ ጥናት ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በዘርፉ የሚደረገው የጥናትና ምርምር ሥራዎች በዋናነት በስነ ምድር መስክ የማዕድንና ቁፋሮ፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዳ የከባቢ አየር ጥናትን ጨምሮ የግብርና መር ኢንዱስትሪን ማሳደግ በሚደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች የቤተ ሙከራው መደራጀት ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል ዶክተር መላቱ።
እንዲሁም የቤተ ሙከራው በዚህ መልኩ መደራጀት ለላቀ ጥናትና ምርምር አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው፥ መምህራንና ተማሪዎች ብዙ ሳይርቁ የዘርፉን የጥናትና ምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል ማለታቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.